የሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ታሪክ
የሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ አጭር ታሪክ
ወደግማሽ ክፍለዘመን የሚጠጋው የሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ታሪክ፣ የኮሌጁን ስኬት ያሳያል፡፡ የሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ (ሀመትኮ) የተመሰረተው በ1969 ዓ.ም. ነው፡፡ ይህ ዓመት በክልሉ አዲስ የትምህርት ተቋማት የተገነቡበት፣ በተለይም የመምህራን ትምህርት የተከፈተበት ነበር፡፡ የሀመትኮ ታሪክ ከኮሌጁ ጋር የተያያዙ ታሪካዊ ሁነቶችን መነሻ በማድረግ በሁለት ወቅቶች ሊከፈል ይችላል፡፡ ይህም፣ የመጀመሪያ ወቅት እና ሁለተኛ ወቅት በመባል ይከፈላል፡፡ የመጀመሪያው ወቅት፣ ከ1969 - 1989 ያለውን ጊዜ የሚመለከት ሲሆን፣ ከ1989 ዓ.ም. በኋላ እስካሁን ያለው ደግሞ ሁለተኛው ወቅት ነው፡፡
የሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ታሪክ፣ የሀዋሳ የመምህራን ትምህርት ተቋም ከተመሰረተበት ከ1969 ዓ.ም. የሚጀምር ነው፡፡ በእዚህ ወቅት ተቋሙ በዋናነት የአንደኛ ደረጃ መምህራንን የማሰልጠን ኃላፊነት ተሰጥቶት ነበር፡፡ ተቋሙ ይዞ የተነሳው መርሃ ግብር እጩ መምህራኑ በተመለመሉበት ቦታ ሄደው እንዲያስተምሩ ለማድረግ ነበር፡፡ በተጨማሪም ተቋሙ በስራ ላይ ስልጠና (በክረምት) መርሃ ግብር የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስራ መሪዎችን ያሰለጥን ነበር፡፡ ተቋሙ በ1969 ዓ.ም. አጋማሽ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚሰሩና የመምህርነትን ስልጠና ሳይወስዱ እያስተማሩ ያሉ የድጎማ መምህራንን ተቀብሎ የአጭር ጊዜ የስራ ላይ ስልጠና ይሰጥም ነበር፡፡ የሀዋሳ መምህራን ትምህርት ተቋም ምስረታ በኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በ1969 ዓ.ም. ካጋጠመ ታሪካዊ ክስተት ጋር የተያያዘ ነበር፡፡ ይህ ዓመት የኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የአንደኛ ደረጃ መምህራንን በሰርተፍኬት ማሰልጠን ያቆመበት ዓመት ነበር፡፡ በመሆኑም፣ በኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ይሰጥ የነበረው የሰርተፍኬት መርሃ ግብር ወደሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ (ቀድሞ ሀዋሳ መምህራን ትምህርት ተቋም ወደሚባለው) ተዘዋወረ፡፡ ይህ መርሃ ግብርም ተቋሙ ወደኮሌጅ እስካደገበት እስከ 1988 ዓ.ም. ድረስ ቀጥሏል፡፡ ወደኮሌጅነት እስካደገበት እስከ 1988 ዓ.ም. ድረስም ተቋሙ ከ18‚779 በላይ መምህራንን በሰርተፍኬት አስመርቋል፡፡
የዲን መልእክት
የሀዋሳ መምህራን ትምህርት የኮሌጅ ዲን መልዕክት
የሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የተመሰረተው በ1969 ዓ.ም. ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ላለፉት 45 ዓመታት በልዩ ልዩ የስልጠና ዘዴዎች መምህራንንና የትምህርት ባለሙያዎችን ተገቢ ዕውቀትና ክህሎት እንዲያገኙ በማድረግ እያፈራ ይገኛል፡፡ እስካሁን በ12+1 ሰርተፍኬት መርሃ ግብር 18‚779 መምህራንን፣ በ12+2 እና በ12+3 በዲፕሎማ የመደበኛና የተከታታይ መርሃ ግብሮች ደግሞ 68‚347 መምህራንን እንዲሁም ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር 434 ተማሪዎችን በትምህርት እቅድና አስተዳደር መስክ በመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ ግብር አስመርቋል፡፡ ኮሌጁ በሀገሪቱ ደረጃ አስተማማኝና ብቁ ተቋም በመሆን፣ የመምህራን ትምህርት ስልጠና የልህቀት ማዕከል ሆኖ ተመርጧል፡፡ኮሌጁ በዓለም አቀፍና በአገር አቀፍ ትብብር የሚታወቅ ሲሆን ለምሳሌም KOICA (Korea International Cooperation Agency), (PIN) People in Need- from the Czech Republic እና UNESCOን ከመሳሰሉ አጋሮች ጋር የተለያዩ የፕሮጀክት ስራዎችን ሰርቷል፡፡ በተጨማሪም BESO, VESO, TDP, WORLD LEARNING PIN, GEQIP, UNESCO እና ከመሳሰሉት ድርጅቶች የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ አግኝቷል፡፡ በተጨማሪም፣ ከ1990ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ በጎ ፈቃደኛ የውጭ አገር ዜጎች በኮሌጁ ውስጥ በማስተማር ስራ ላይ ተሳትፈዋል። በአገር አቀፍ ደረጃም ከኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ዝግጁነት ኢኒሼቲቭ (ESRI) ጋር በመተባበር ቀዳማይ የልጅነት እንክብካቤና ትምህርት ክፍልን በኮሌጁ ድጋፍ ከሚደረግላቸው የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶች ጋር በማቀናጀት የአቅም ግንባታ ፕሮጀክትን በማከናወን ላይ ይገኛል።
አካዳሚክ
አዳዲስ ዜናዎች

Rosu hiiqqamme sissate loonsanni hee'noonni loosira balaxote rosi aana tungoonni illacha…

የሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በአዲሱ የትምህርት ሮድማፕ መሰረት ላለፉት 2 አመታት በቅድመ አንደኛ ትምህርት 12+2 ዲፕሎማ ደረጃ ስልጠና ሲከታተሉ…

HAWALLE HAGIIDHINOOMMO!
Hawaasi Rosiisaanote Rosi/Kolleeje 25kki doycho maassamaano…

Kolleejenketi 2016 M.D bocu diri mixote jeefishsha SDQM Rosu Biirora shiqinshe keennoonni.…
ራዕይ
ራዕያችን፣ እ.ኤ.አ 2022 ዓ.ም በትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ እውቅና ያለው ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሆኖ የአጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና አሁን ያሉትንም ሆነ ወደፊት የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ለመወጣት የማህበረሰባችንን ህይወት ለማሻሻል የሚያግዙ ብቁ የትምህርት ባለሙያዎችን በሚፈለገው መጠን ሲያፈራና ትምህርት ቤቶችን ሲያዘምን ማየት ነው፡፡
ተልዕኮ
የእኛ ተልእኮ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር እና የትምህርት መሪ ልማት በፖሊሲ መር፣ ልምድን መሰረት ባደረገ፣ በሚገባ በተጠና፣ በመስክ የተረጋገጠ እና በዘመናዊ የጥበብ አዳዲስ አቀራረቦች፣ ስልቶች፣ ዘዴዎች እና ቴክኖሎጂዎች ጥራትን እና የላቀ ደረጃን እውን ማድረግ ነው።
እሴቶች
- ሙያዊ ሥነ ምግባርን ማክበር
- ሙያዊ ተጠያቂነት
- አደራ
- ግልጽነት
- የህዝብን ጥቅም ማገልገል
- ታማኝነት
- የሚማር ማህበረሰብ መፍጠር