Skip to main content

ራዕይ

ራዕያችን፣ እ.ኤ.አ 2022 ዓ.ም በትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ እውቅና ያለው ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሆኖ የአጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና አሁን ያሉትንም ሆነ ወደፊት የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ለመወጣት የማህበረሰባችንን ህይወት ለማሻሻል የሚያግዙ ብቁ የትምህርት ባለሙያዎችን በሚፈለገው መጠን ሲያፈራና ትምህርት ቤቶችን ሲያዘምን ማየት ነው፡፡

ተልዕኮ

ተልዕኳችን የመጀመሪያና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርን ጥራትና ብቃት እንዲሁም የትምህርት አመራር ልማትን በፖሊሲ መር፣ በተገቢ ልምድ፣ በሚገባ በተፈተሸና በመስክተረጋገጠበፈጠራዊ አቀራረቦች፣ ስልቶች፣ ዘዴዎችና ቴክኖሎጂዎች አማካይነት እውን ማድረግ ነው። ይህም በቅድመ አገልግሎት ስልጠና፣ በስራ ላይ ስልጠና እና በአጫጭር ስልጠናዎች የሚተገበር ሲሆን የሚመለከታቸው የትምህርት ሴክተር ባለድርሻ አካላትና አጠቃላይ ማህበረሰቡ እንዲያውቁትና እንዲሳተፉበት ማድረግ ነው።

ዋና ዋና እሴቶች

  • ሙያዊ ስነምግባርን ማክበር
  • ሙያዊ ተጠያቂነት
  • መተማመን
  • ግልጸኝነት
  • ለህዝብ ጥቅም መስራት
  • ቅንነት
  • የሚማር ማህበረሰብ መፍጠር
  • ጊዜን በሚገባ ማክበር
  • ለትምህርት ፖሊሲ እገዛ ሊያደርጉ የሚችሉ ጥናትና ምርምሮችን መስራት
  • የለውጥ ሀዋርያ መሆን
  • የኮሌጁን ታይነት (ታዋቂነት)ማላቅ
  • ማጭበርበርን መቃወም

ግቦች

  • ትምህርት ዝግጅት፣ በማስተማር፣ በምርምር፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በአመራር ብቃት ያላቸውን የትምህርት ባለሙያዎች ማዘጋጀት፤
  • በማስተማር፣ በመማርና የትምህርት ውጤቶችን ምዘና በምርምር፣ በትምህርትና በቴክኖሎጂ በመመዘን የትምህርት ውጤቶችን በማሻሻል ረገድ ሰፊ እውቅና ያለው አመራር መስጠት፤
  • የመምህራንን፣ የሰራተኞችንና የተማሪዎችን ብዝሃነት፣ የማህበራዊ ፍትህና የዲሞክራሲያዊ ዜግነት ቁርጠኝነትን ማሳደግ፤
  • በትምህርት ቤቶች፣ማህበረሰቡ መካከልና በስራ ከባቢዎች በትምህርት ስራ መሻሻል ላይ ትኩረት ያደረገ ትብብርና ሙያዊ ግንኙነት ከትምህርት ቤቶች፣ድርጅቶችና ሌሎች ተቋማት ጋር ለማጎልበት አመራር መስጠት፤
  • በኮሌጅና በክላስተር /ቤቶች ሁሉን አቀፍ ደጋፊ የስራ ሁኔታን ማረጋገጥ፤
  • የኮሌጁን አስተዳደር ውጤታማነትና ብቁነት ማሳደግ፤