Skip to main content
slide

የማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ

 እንኳን ወደ ሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ በደህና መጡ! 

በሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ቀደም ብለው ከተቋቋሙት ዘርፎች መካከል አንዱ የማህበራዊ ሳይንስ ሲሆን የሚከተሉትን ዓላማዎች ለማሳካት ያለመ ነው፡፡

ስለመብቶቻቸውና ግዴታዎቻቸው በቂ ግንዛቤ ያላቸው፣ ለማህበረሰባቸው፣ ለሀገራቸውና ለአለም አዎንታዊ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ እንዲሁም ጠንካራ የመደራደር ችሎታ፣ ጥልቅ እውቀትና የሀገር ፍቅር ስሜት ያላቸው ዜጎችን ማፍራት ነው። ይህም ሰብአዊ መብቶችንና ዲሞክራሲያዊ መርሆችን የሚጠብቅና እርስ በእርሱ የሚከባበር ማህበረሰብ እንዲፈጠር ያበረታታል።

በፍትህ፣ በመቻቻል በብዝሃ ባህልና በህግ የበላይነት የሚያምኑ አለም አቀፍ ተወዳዳሪና ተባባሪ ተማሪዎችን ማፍራት ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ያለፉ ታሪካዊ ክስተቶችን ከወቅቱ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ግብረ ገባዊ ጉዳዮች ጋር በማስተሳሰር የማህበረሰቡን ዋና ዋና እሴቶች ያካተተ የጋራ ታሪክ እንዲኖር ይደግፋል፡፡

ኢትዮጵያጥንታዊው፣ በመካከለኛውናዘመናዊ ስልጣኔዎች በአፍሪካ ቀንድ፣ በአጠቃላይ አፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለነበራት የመንግስት አደረጃጀቶችና ጉልህ የፖለቲካ ተሳትፎ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት በሀገር ታሪክና በሀገር ግንባታ ላይ ኩራት የሚሰማው ትውልድ እንዲፈጠር አስተዋጽኦ ያደርጋል።

ከዚህም በላይ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስልቶችን፣ የአየር ንብረት ለውጥ መንስኤዎችንና የሚያስከትሏቸውን መዘዞች በማስተዋወቅና በአካባቢ፣ በባህል፣ በሕዝብ ብዛት በአሰፋፈር መካከል ያለውን ግንኙነት በማስተማር ስለአካባቢ ያለን ግንዛቤ ለማዳበር ጥረት ያደርጋል። የመሬት አቀማመጥ ባህርያትንናአፈጣጠር ሂደቶችን ግንዛቤ በማጎልበት፣ በቱሪዝም ልማት ላይ ተፅእኖ ያላቸውን ቁልፍ ነገሮች በመለየትና በመረዳት ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ እድገት መሰረት ይጥላል።

በመጨረሻም የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማሻሻል፣ የማህበረሰብን ችግር ለመፍታት፣ የሰው ልጅን እውቀት ለማሳደግ፣ ሳይንስን ለማበልጸግ፣ የፈጠራ ስራን ለማስተዋወቅ፣ ሳይንሳዊ ግኝቶችን ለማህበረሰቡ ለማድረስ ጥናትና ምርምር ያደርጋል፡፡  በዜግነት፣ በስነ ምግባር፣ በሀገር ፍቅር፣ በብዝሃ ባህልና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ስልጠና በመስጠት፣ በታሪካዊ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ የውይይት መድረኮችን በማመቻቸት፣ ታሪካዊ ርእሰ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማዘጋጀትና ብዙ ሰው እንዲያነባቸው በማስተዋወቅ ለማህበረሰብ አገልግሎት ይሰጣል፡፡

በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ስር ያሉ የትምህርት ክፍሎች የሚከተሉትን ናቸው፤

1. የስነ ዜጋ ትምህርት ክፍል

2. የግብረ ገብ ትምህርት ክፍል

3. የህብረተሰብ ትምህርት ክፍል

4. የታሪክና የቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል

5. የጂኦግራፊና የአካባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል

  1. በዘርፉ ስር የሚገኝ የሰው ኃይል

በዘርፉ ስር፣ ሰባት በስነ ዜጋና በግብረ ገብ፣ ሶስት በታሪክና ቅርስ አስተዳደር፣ አራት በጂኦግራፊ እና የአካባቢ ጥናት ትምህርት ክፍሎች በአጠቃላይ 14 MA ዲግሪ ያላቸው መምህራን አሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ሶስቱ በተለያዩ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የዶክትሬት ዲግሪ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡

  1. በዘርፉ ስር የሚገኝ ቁሳዊ ሀብት

በዘርፉ ስር ያሉ ሁሉም የትምህርት ክፍሎችከፍተኛ መጠን ቁሳዊ ሀብት አላቸው፤ ከእነዚህም መካከል በደንብ የተደራጁ ሞዴል መማሪያ ክፍሎች፣ በቂ መጠን ያለው የመማሪያና ማስተማሪያና እንዲሁም የማጣቀሻ መፅሀፎች ተጠቃሾች ናቸው።

መብራቱ ማሞ ዳሳ (ኤም ኤ)

የማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ኦፊሰር

+251912110156