Skip to main content

የማህበረሰብ አገልግሎት

የሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ካሉት ሶስት ዋና ተልዕኮዎች የማህበረሰብ አገልግሎት አንዱ ነው፡፡ ከምስረታው ጀምሮ ኮሌጁ በርካታ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን ሲሰራ ነበር፤ እየሰራም ይገኛል፡፡ የኮሌጁ የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራት የአካባቢውን ምህበረሰብ ኑሮ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ልያሻሽሉ ከሚችሉ የቁሳቁስ ድጋፍ ጀምሮ መሰረተልማት ግንባታ ስራዎች ድረስ ልሆን ይችላል፡፡ ከበርካታ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ጥቂቶቹ ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡

  • ኮሌጃችን በሲዳማ ብ//ክ/መ ማዕከላዊ ዞን ዳሌ ወረዳ ሶያማ ቀበሌ አንድ ሞደል የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤት ከ7,000,000.00 (ሰባት ሚሊዮን) ብር በላይ በሆነ ወጪ እያስገነባ ይገኛል፡፡ ግንባታው ፋይናንስ የሚደረገው የኮሌጃችን መላው ማህበረሰብ ባዋጣው የአንድ ወር ደመወዝ መዋጮ እና ከኮሌጁ የውስጥ ገቢ ነው፡፡
  • “Sidaamu-Afoo Hanafaano Borreessaanora” በሚል ርዕስ በኮሌጁ የተዘጋጀው ከ2400 በላይ መጽሐፍ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን የማንበብና የመጻፍ ችሎታን ለማሳደግ ያግዝ ዘንድ ለክልሉ ትምህርት ቢሮ ተበርክቶ ስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡
  • ከ15 በላይ ያገለገሉ ኮምፒዩተሮች፣ የሳይንስ የሙከራ የተግባር ትምህርትን ለማበረታታት ከ50 በላይ የተለያዩ ኬሚካሎች፣ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች እና የሳይንስ ኪት ለተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተበርክቷል፡፡  
  • ለሆጎባ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ210 በላይ ወንበሮችን በማበርከት የመማሪያ ክፍልን ያደራጀን ሲሆን፤ ለሀዋሳ ማረሚያ ተቋም፣ ለዳካ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ለአዲስ ዘመን 1ኛ ደረጃ  ት/ቤት፣ ለሐዌላ ሊዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለእያንዳንዳቸው 50 ወንበሮች ተበርክቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጠረጴዛዎችና መደርደሪያዎችም ተበርክዋል፡፡
  • አቅም ሌለላቸው 40 ቤተሰቦች ከ36,000.00 (ሰላሳ ስድስት ሺህ ብር) በላይ ወጪ የአንድ አመት የህክምና ኢንሹራንስ ግዥ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
  • ከልክሉ መምህራን ማህበር አመታዊ የትምህርት ጉባዔ የ50,000.00 (አምሳ ሺህ) ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡

እነዚህ የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራት  በዚህ አመት የተከናወኑ ዋና ዋና ሲሆኑ ከበርካታ ስራዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በዚህ አጋጣሚ የተለያዩ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን የሚያከናውኑ አገርአቀፍና አለምአቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች ከኮሌጃችን ጋር በአጋርነት እንዲሰሩ የአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡