Skip to main content

የመምህራን ልማት ጉዳዮች ምክትል ዲን ቢሮ

ኮሌጁ ሁለት ምክትል ዲኖች አሉት። አንደኛው ቀደም ሲል ምክትል ዲን እና መምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማትና አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት ባለቤት ይባል የነበረ ሲሆን አሁን ግን የመምህራን ልማት ጉዳዮች ምክትል ዲን በመባል የሚጠራው ነው። በብቃቱ ተወዳድሮ የሚሾመው የመምህራን ልማት ጉዳዮች ምክትል ዲን፣ ዋና ዲኑን በአካዳሚክ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ እገዛ ያደርጋል የመምህራን ልማት ጉዳዮች ምክትል ዲን ዋና ዋና ተግባራት በኮሌጁ ህግ ውስጥ ተዘርዝረው ተገልጸዋል። በመምህራን ልማት ጉዳዮች ምክትል ዲን ቢሮ ስር የሚካተቱት የስራ መደቦች የአካዳሚክ ዘርፍ አስተባባሪዎች፣ የትምህርትና ስልጠና አስተባባሪ፣ የፕራክቲከምና የት/ቤት ትስስር አስተባባሪ፣ የተከታታይ ትምህርትና የተማሪዎች አገልግሎት ማስተባበሪያ እንዲሁም ሬጅስትራርና የአሉምናይ አገልግሎቶች ናቸው፡፡

በአሁኑ ጊዜ በሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ እየተሰጡ ያሉት የዲግሪ ደረጃ የትምህርት ፕሮግራሞች፡-

  1. የሲዳሙ አፎ ትምህርት ክፍል
  2. የአማርኛ ትምህርት ክፍል
  3. የእንግሊዝኛ ትምህርት ክፍል
  4. የሂሳብ ትምህርት ክፍል
  5. የአጠቃላይ ሳይንስ ትምህርት ክፍል
  6. የአካባቢ ሳይንስ ትምህርት ክፍል
  7. የማህበራዊ ጥናቶች ትምህርት ክፍል
  8. የስነ ዜጋና ስነምግባር ትምህርት ክፍል
  9. የግብረ ገብ ትምህርት ክፍል
  10.  የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል
  11.  የክወናና የእይታ ጥበባት ትምህርት ክፍል
  12.  የኢንፎርሜሽንና የመገናኛ ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል
  13.  የሙያና የቴክኒክ ትምህርት ክፍል

በተጨማሪም ቀዳማይ የልጅነት እንክብካቤና ትምህርት (ECCE) 12+ 2 በዲፕሎማ ደረጃ ይሰጣል። እነዚህ የአካዳሚክ መርሃ ግብሮች በመደበኛ እንዲሁም በቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብሮች ይሰጣሉ፡፡ ኮሌጃችን 210 የትምህርት ዘርፍ ባለሙያዎች ያሉት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 91% የሚሆኑት የማስተርስ ዲግሪ እንዲሁም 4.5% ያህሉ ደግሞ ፒ ኤች ዲ ያላቸው ናቸው። በአሁኑ ወቅትም 38 በላይ የኮሌጃችን መምህራን የፒ ኤች ዲ ዲግሪያቸውን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በመከታተል ላይ ይገኛሉ።

የመምህራን ልማት ጉዳይ ምክትል ዲን ቢሮ

ስልክ፡- 251462202272