የተከታታይ ትምህርትና የተማሪዎች አገልግሎት ማስተባበሪያ (CEP)
የተከታታይ ትምህርትና የተማሪዎች አገልግሎት ማስተባበሪያ፣ ከመደበኛና ተከታታይ ፕሮግራሞች ጋር የተያያዙ በርካታ ተግባራትና ኃላፊነቶች አሉት። ከእነዚህም መካከል ተማሪዎች የመመራትና የምክክር አገልግሎት ማግኘታቸውን ያረጋግጣል፤ የተማሪዎች መማክርት አደረጃጀትን ያመቻቻል፤ የተማሪዎችን የዲሲፕሊን ጉዳዮችን ይከታተላል፤ በዲስፒሊን ኮሚቴ ውስጥም አብሮ ይሰራል፡፡
ተማሪዎች የኮሌጁን የአካዳሚክና የአስተዳደር ደንቦችን በሚመለከት ተገቢውን ገለፃና ግንዛቤ ማግኘታቸውን ያረጋግጣል። በተጨማሪም ከሌሎች ከሚመለከታቸው የኮሌጁ ቢሮዎች ጋር በመተባበር ማህበራዊና ባህላዊ እንቅስቃሴዎችን ያከናውናል፡፡
የመደበኛና የተከታታይ መርሃ ግብር ተማሪዎች ከበድ ያሉ የማህበራዊና የጤና ችግሮች ሲገጥማቸው ከትምህርት ክፍልና ከስትሪሞች ጋር በመመካከር ፈቃድ ይሰጣል፡፡ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ለመመልመል የሚያግዝ የመግቢያ ፈተና ዝግጅትን ያስተባብራል፤ የጊዜ ሰሌዳ በማዘጋጀትም የትምህርት ስራ በጊዜ ሰሌዳው መሰረት በወቅቱ መጀመሩን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል።
በተጨማሪ ለመደበኛና ለተከታታይ ትምህርት መርሃ ግብር ተማሪዎች በአካዳሚክ ጉዳዮች ላይ እንዲያማክሩ መምህራንን ይመድባል፤ ውጤታማነቱንም ይከታተላል፡፡ የፕራክቲከም ኮርሶችን ስራ ያስተባብራል፤ በዚህም በፕራክቲከም ስራ ላይ ለሚሳተፉ የኮሌጅ መምህራንንና ተማሪዎች እንዲሁም ተማሪዎች ለልምምድ ለሚሄዱባቸው አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን፣ ምክትል ርዕሰ መምህራንና ተሳታፊ መምህራን ገለፃ ይሰጣል። የአካዳሚክ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች የማሻሻያ ፕሮግራሞችን ያመቻቻል፤ የአካዳሚክ እና የዲሲፕሊን ሪከርዶችን ይይዛል፤ ሁሉንም የ “F” ውጤቶች ለአካዳሚክ ኮሚሽን ከነምክንያቱ ያቀርባል። ከእያንዳንዱ ምዘና በኋላ ለመደበኛ እና ለተከታታይ መርሃ ግብር ተማሪዎች በወቅቱ ተገቢ ግብረ መልስ መሰጠቱን ያረጋግጣል።
ታፈሰ ታደለ - የተከ/ትም/ተማ/አገ/ኦፊሰር
+251919307541