የአስተዳደርና ልማት ጉዳዮች ምክትል ዲን ቢሮ
ወደሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ድረ ገጽ እንኳን ደህና መጡ! አላማችን፣ የአስተዳደርና ልማት ጉዳዮች ምክትል ዲንን እንዲሁም ተግባሮቹንና በስሩ ያሉትን ክፍሎች ማስተዋወቅ ነው። የተለየ ነገር ለማግኘት፣ አዲስ ነገር ለመፍጠር፣ ከእኛ ጋር ለመግባባት፣ ለመሳተፍና ለመተባበር ነፃነት ይሰማዎ።
የሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉና በተገቢ ሁኔታ ከተደራጁ ኮሌጆች አንዱ ሲሆን ላለፉት 45 ዓመታት በማስተማር፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት ላይ ቆይቷል፡፡ በ1976 ዓ.ም የሀዋሳ መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም፣ በ1996 ዓ.ም ደግሞ የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሆኖ ተመስርቷል፡፡ ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮም ለክልላችንና ለሀገራችን መምህራንና የትምህርት አመራሮችን በማሰልጠን ላይ ይገኛል።
የኮሌጁ ተቋማዊ መዋቅር ለኮሌጁ ዲን ተጠሪ የሆኑ የአካዳሚክ እንዲሁም የአስተዳደርና ልማት የተሰኙ ሁለት ምክትል ዲኖችን የያዘ ነው፡፡ ከእነዚህም አንዱ የሆነው የአስተዳደርና ልማት ምክትል ዲን ቢሮ የኮሌጁን ዋና ግብ ለማሳካት ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ይህ ቢሮ የሰው ሃይል የማሰባሰብ፣ የፋይናንስ ሃብትና የግዥ ሂደቶችን የመቆጣጠር እንዲሁም የሰውና የቁሳቁስ አጠቃቀምን የመቆጣጠር ሃላፊነት አለበት። የላቀ ብቃትና ፈጠራን የሚያጎለብት የትምህርት አካባቢ ለመፍጠርም ይተጋል፡፡
በተጨማሪም ቢሮው የኮሌጁን አላማ ከግብ ለማድረስ በስሩ ካሉት ዘርፎች ጋር በመተባበር፣ ለአንድ አላማ በመቆምና በቡድን በመስራት የኮሌጅ ተማሪዎችንና የማህበረሰብ አባላትን ለማገልገል ያለመ ነው። የቡድን ስራም በማንኛውም ዘርፍ ለስኬት አስፈላጊ መሆኑን እናምናለን።
በስራችን ላይ ያልዎትን ማንኛውንም ሀሳብ ወይም አስተያየት ከስር በቀረበው የኢሜል አድራሻ ቢጽፉልኝ በደስታ እቀበላለሁ፡፡ ሁልጊዜም ለተገልጋዮች እርካታ ቅድሚያ እንሰጣለን! በድጋሚ ወደድረ ገጻችን እንኳን ደህና መጡ!
ብርሃኑ ማጆ
የአስተዳደርና ልማት ጉዳዮች ምክትል ዲን
ሞባይል ስልክ፡- +251-912107678