እንኳን ወደ ሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሬጅስትራርና አሉምናይ ጽ/ቤት በደህና መጣችሁ!
በሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የሬጅስትራር ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ረገድ ጉልህ ሚና ከሚጫወቱት የኮሌጁ ዋና ዋና ጽ/ቤቶች አንዱ የሆነው ሬጅስትራርና አሉምናይ ጽ/ቤት ነው።
ሬጅስትራር ሁለት ቢሮዎች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ዋናው ቢሮ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የማህደር ክፍል ነው።
- ዋናው ቢሮ ከተለያዩ ቦታዎች የሚመጡ ጉዳዮችን ያስተናግዳል፡፡ ለምሳሌ የተለያዩ የትምህርት ማስረጃዎችን የመመዝገብና ትክክለኛነታቸውን ማረጋገጥ፤
- የማህደር ክፍል ከዋናው ቢሮው የሚመጡ የተለያዩ ተግባራትን የማከናወን ኃላፊነት አለበት። ከእነዚህም መካከል፡-
- የተማሪዎችን የምዝገባ ሂደት ማከናወን
- ተማሪዎችን በቡድን መመደብ
- ማስተር ሺት፣ ኦፊሻል፣ የተማሪዎች ዝርዝር፣ ውጤቶች እና የመሳሰሉትን ማዘጋጀት
- ኮርሶችን መጨመር እና መቀነስ
- በተለያየ ምክንያት ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎችን ጉዳይ ማስፈጸም
ተልዕኮ
የኮሌጁ ሬጅስትራርና አሉምናይ ጽ/ቤት በቅንነት፣ በትክክለኛነት፣ በብቃት፣ በቅልጥፍና፣ ሚስጥራዊና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ አገልግሎት ማቅረብ ነው፡፡ ከመምህራን፣ ከተማሪዎች፣ ከሰራተኞችና ከቀድሞ ተመራቂዎች ጋር በመተባበርና ቴክኖሎጂን በመጠቀም፣ ለምዝገባና ለአካዳሚክ መዛግብት የተቀናጀ አገልግሎት በመስጠት ቀዳሚ ለመሆን እንተጋለን።
‹ራዕይ
ለተማሪዎቻችን ምቹ የሆነ አካባቢና ሙያዊ ልህቀት የሚታይበት ክፍል ለመሆን እንፈልጋለን።
እሴቶች
- የአካዳሚክ መዛግብትን ሚስጥራዊነትና ደህንነት መጠበቅ
- ለመሻሻልና ለአዳዲስ ፈጠራዎች ከሌሎች ጋር መተባበር
- ለደንበኞቻችን የበለጠ ተደራሽ መሆን እንድንችል ቴክኖሎጂን መጠቀም
- ከኮሌጁ ማህበረሰብ ጋር የተያያዙ ሁሉንም ቴክኖሎጂዎች ከተማሪ መረጃ ስርዓት ጋር በተገናኘ ድጋፍ መስጠት (ለምሳሌ፡- የተማሪዎች ሬጅስትራር ፖርታል፣ የአካዳሚክ ሰራተኞችና የቀድሞ ተማሪዎች የተለያዩ የምዝገባ ወይም የሰነድና መረጃ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ)
• ተንከባካቢና ተነሳሽነት ያላቸው ሰራተኞችን ማፍራት
• የቡድን ስራን ማበረታታት።
• ስነ ምግባራዊ መሆን
ጌታቸው ቦጋሌ (ኤም ኤ)
የሬጅስትራርና አሉምናይ ጽ/ቤት ኦፊሰር
+251913426108