የተከታታይ ትምህርትና የተማሪዎች አገልግሎት ማስተባበሪያ (CEP)
የተከታታይ ትምህርትና የተማሪዎች አገልግሎት ማስተባበሪያ፣ ከመደበኛና ተከታታይ ፕሮግራሞች ጋር የተያያዙ በርካታ ተግባራትና ኃላፊነቶች አሉት። ከእነዚህም መካከል ተማሪዎች የመመራትና የምክክር አገልግሎት ማግኘታቸውን ያረጋግጣል፤ የተማሪዎች መማክርት አደረጃጀትን ያመቻቻል፤ የተማሪዎችን የዲሲፕሊን ጉዳዮችን ይከታተላል፤ በዲስፒሊን ኮሚቴ ውስጥም አብሮ ይሰራል፡፡
ተማሪዎች የኮሌጁን የአካዳሚክና የአስተዳደር ደንቦችን በሚመለከት ተገቢውን ገለፃና ግንዛቤ ማግኘታቸውን ያረጋግጣል። በተጨማሪም ከሌሎች ከሚመለከታቸው የኮሌጁ ቢሮዎች ጋር በመተባበር ማህበራዊና ባህላዊ እንቅስቃሴዎችን ያከናውናል፡፡
የመደበኛና የተከታታይ መርሃ ግብር ተማሪዎች ከበድ ያሉ የማህበራዊና የጤና ችግሮች ሲገጥማቸው ከትምህርት ክፍልና ከስትሪሞች ጋር በመመካከር ፈቃድ ይሰጣል፡፡ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ለመመልመል የሚያግዝ የመግቢያ ፈተና ዝግጅትን ያስተባብራል፤ የጊዜ ሰሌዳ በማዘጋጀትም የትምህርት ስራ በጊዜ ሰሌዳው መሰረት በወቅቱ መጀመሩን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል።
በተጨማሪ ለመደበኛና ለተከታታይ ትምህርት መርሃ ግብር ተማሪዎች በአካዳሚክ ጉዳዮች ላይ እንዲያማክሩ መምህራንን ይመድባል፤ ውጤታማነቱንም ይከታተላል፡፡ የፕራክቲከም ኮርሶችን ስራ ያስተባብራል፤ በዚህም በፕራክቲከም ስራ ላይ ለሚሳተፉ የኮሌጅ መምህራንንና ተማሪዎች እንዲሁም ተማሪዎች ለልምምድ ለሚሄዱባቸው አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን፣ ምክትል ርዕሰ መምህራንና ተሳታፊ መምህራን ገለፃ ይሰጣል። የአካዳሚክ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች የማሻሻያ ፕሮግራሞችን ያመቻቻል፤ የአካዳሚክ እና የዲሲፕሊን ሪከርዶችን ይይዛል፤ ሁሉንም የ “F” ውጤቶች ለአካዳሚክ ኮሚሽን ከነምክንያቱ ያቀርባል። ከእያንዳንዱ ምዘና በኋላ ለመደበኛ እና ለተከታታይ መርሃ ግብር ተማሪዎች በወቅቱ ተገቢ ግብረ መልስ መሰጠቱን ያረጋግጣል።
ታፈሰ ታደለ - የተከ/ትም/ተማ/አገ/ኦፊሰር
+251919307541
የትምህርት ዘርፍ መልዕክት (Message from the Education Stream) እንኳን ወደ ሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ድረ ገጽ በደህና መጡ። የኮሌጃችን ዋና ዓላማ በሀገራችን ውስጥ በትምህርት ስልጠና ላይ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ነው። ለዚህም በጥናት ላይ የተመሰረተ ችግር ፈቺ አገልግሎት፣ ተማሪን ያማከለ ስልጠናና የማህበረሰብ አገልግሎት በመስጠት ቁርጠኛነቱን እያሳየ ነው። በሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በአካዳሚክ ዘርፍ ውስጥ ካሉት አንጋፋ ዘርፎች አንዱ የትምህርት ዘርፍ ሲሆን በመማር ማስተማር ዘርፍ መሰረታዊ እውቀትን ይሰጣል። እ.ኤ.አ. በ1969 ዓ.ም የተመሰረተው የትምህርት ዘርፍ ሰልጣኞችን ከሰርተፍኬት እስከ ዲግሪ መርሃ ግብሮች ሲያስመርቅ ቆይቷል፡፡ ዘርፋችን የአካቶ መማር ስልቶች፣ የመማሪያ ክፍል አስተዳደር፣ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ክለሳ፣ ስነ ልቦናዊ ዝግጁነት፣ የማስተማር ስነ ዘዴዎች እንዲሁም የህፃናት ክብካቤና እድገት ላይ ትኩረቱን በማድረግ በሰባት የትምህርት ክፍሎች ሰልጣኝ መምህራንን ያሰለጥናል፡፡
ዘርፋችን፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ማህበረሰቡ የሚሳተፉበት፣ ተማሪዎችን ማዕከል ያደረገ ትምህርት፣ ባህልን ከግምት ያስገባ የማስተማር ስነ ዘዴን፣ ሳይንሳዊ ግኝትን፣ ጠንካራ ድጋፍንና ማህበረሰብን መሰረት ያደረገ ተሳትፎ የሚታይበትን ምቹ የትምህርት አካባቢ ያበረታታል። እ.ኤ.አ ከ1969 ዓ.ም ጀምሮ ኮሌጃችን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሀገሪቱን እያገለገሉ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ የትምህርት ባለሙያዎችን አሰልጥኗል።
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮና በአካባቢ ትምህርት ቤቶች ላሉ አመራርና ባለሙያዎች ቁልፍ የሰው ሃይል ምንጭም ሆነናል። በዘርፋችን፣ ታታሪ፣ ንቁ፣ ልምድና እውቀት ካላቸው መምህራን እና አመራሮች ጋር በመተባበር በሁሉም መስክ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ እንተጋለን። ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የሀዋሳ መምህራን ተምህርት ኮሌጅ የልህቀት ማዕከል ሆኖ እውቅና ተሰጥቶት ለማህበረሰቡም ሆነ በኮሌጁ እና በአካባቢው ላሉ የትምህርት እድል እየሰጠ ነው። የሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅን እንድትጎበኙና የምትፈልጉትን መረጃ በዚህ ድረ ገጽ እንድታገኙ እንጋብዛለን፤ ድረ ገጹን እንደሚጎበኙም ተስፋ እናደርጋለን።
በትምህርት ዘርፉ ስር ስላሉ መምህራን መረጃ
ተ.ቁ |
የትምህርት ክፍል |
ወንድ |
ሴት |
ድምር |
የመጀመሪያ ዲግሪ |
ሁለተኛ ዲግሪ |
ሶስተኛ ዲግሪ |
የሶስተኛ ዲግሪ ሁኔታ |
1 |
የትምህርት እቅድና አስተዳደር |
5 |
1 |
6 |
|
3 |
3 |
(እጩዎች) |
2 |
ስርዓተ ትምህርት |
10 |
4 |
14 |
|
9 |
5 |
(እጩዎች) |
3 |
ስነ ልቦና |
14 |
1 |
15 |
1 |
8 |
6 |
(እጩዎች) |
4 |
ልዩ ፍላጎት |
6 |
1 |
7 |
|
6 |
1 |
(እጩ) |
5 |
ቅድመ አንደኛ |
2 |
2 |
4 |
|
3 |
1 |
(እጩ) |
6 |
የኢንፎርሜሽንና ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂ |
6 |
3 |
9 |
4 |
4 |
1 |
(እጩ) |
7 |
የጎልማሶች ትምህርት |
4 |
0 |
4 |
4 |
|
||
|
ጠቅላላ |
47 |
12 |
59 |
5 |
37 |
17 |
59 |
መብራት በቀለ (ኤም.ኤ)
የትምህርት ዘርፍ ኦፊሰር
ሞባይል ስልክ፡- +251949267202