Skip to main content
slide

የስነ ውበት እና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ዘርፍ

መግቢያ

የስነ ውበት እና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ዘርፍ ከተቋቋመ ከሃያ ዓመታት በላይ ያስቆጠረና በሀዋሳ የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ካሉና ረዘም ያለ ጊዜ ካስቆጠሩ ዘርፎች አንዱ ነው። በመጀመሪያ ትምህርት ክፍሉ ጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርትን ብቻ ያቀፈ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ከሙዚቃና ከስነ ጥበብ ክፍሎች ጋር ተዋህዶ የስነ ውበትና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ዘርፍን ፈጠረ። ከተወሰኑ ዓመታት በኋላም እነዚህ የትምህርት ክፍሎች በዘርፉ ውስጥ ራሳቸውን የቻሉ የትምህርት ክፍል ሆኑ።

በአሁኑ ጊዜም ዘርፉ ሁለት የትምህርት ክፍሎችን ማለትም የእይታና የክወና ጥበባት እንዲሁም የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ክፍሎችን በስሩ አቅፎ ይዟል፡፡

የሰው ኃይል

በአሁኑ ጊዜ፣ዘርፉ ውስጥ በአጠቃላይ 13 መምህራን ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ስድስቱ በጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ክፍል ውስጥ ሲገኙ ቀሪዎቹ ሰባቱ ደግሞ በክወናና የዕይታ ጥበባት ትምህርት ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ከፆታ አንፃርም ዘጠኝ ወንዶችና አራት ሴት መምህራን ናቸው፡፡

 

ቁሳዊ ሀብት

በዘርፉ ውስጥ ያሉት ሁለቱም የትምህርት ክፍሎች በቂ የሆነ የቁሳቁስ ሀብት አላቸው። ይኸውም የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ክፍል የራሱ ጂምናዚየም፣ ሞዴል የማስተማሪያ ክፍልና በቂ የመጫወቻ ስፍራዎች አሉት። የክወና እና የእይታ ጥበባት ትምህርት ክፍልም የስነ ጥበብ እና የሙዚቃ ማስተማሪያ ሞዴል መማሪያ ክፍሎች፣ የኤግዚቢሽን ማሳያ ቦታና የተለያዩ የሙዚቃና የስነ ጥበብ መለማመጃ መሳሪያዎች አሉት።

ቶማስ ገብሬ  (ኤም ኤስ ሲ)

የጤ/ሰ/ማና ኤስቴቲክስ እስትሪም ኦፊሰር