
የቋንቋ ዘርፍ
የቋንቋ ዘርፍ፣ በሀዋሳ የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ውስጥ በመደበኛና የስራ ላይ ስልጠና የሚሰጥ ነው። ሲዳሙ አፎ፣ አማርኛ እና እንግሊዝኛ የሚባሉ ሶስት የትምህርት ክፍሎችን በስሩ አቅፎ የያዘ ሲሆን እያንዳንዱ ክፍልም የየራሱ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ ኮርሶችና የተለያዩ ተግባራት አሉት። የሲዳሙ አፎ ትምህርት ክፍል በስሩ የሲዳማ ባህል ጥናት ማዕከልን፣ የድራማና ስነ ጽሁፍ ክበቦችን ይዟል፡፡ የአማርኛ ትምህርት ክፍልም የድራማና ስነ ጽሁፍ ክበቦችን ይዟል፡፡ የእንግሊዘኛ ትምህርት ክፍል ደግሞ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከል (ኤሊክ) እና የድራማና ስነ ጽሁፍ ክበቦችን ይዟል፡፡ የትምህርት ዘርፉ መሪ ቃል ‹‹ለማህበረሰባችን ብቁና ውጤታማ የቋንቋ መምህራንን ማፍራትና ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠት የላቀ ስራ መስራት›› የሚል ነው።
ሉተር ባልቻ (ኤም ኤ)
የቋንቋ ዘርፍ ኦፊሰር
+251924035773