Skip to main content

 

slide

 

የሂሳብ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ

 

  እንኳን ወደሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ድረ ገጽ በደህና መጡ!

ዳራ

በሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ውስጥ ካሉ ዘርፎች መካከል አንዱ የሂሳብ እና ተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ነው። ይህ ዘርፍ ብቃት ያላቸው፣ ስራቸውን አክባሪና ስነ ምግባርን የተላበሱ ባለሙያዎችን ለሂሳብና ሳይንስ ትምህርት በማሰልጠን ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው። እነዚህ ባለሙያዎችም ጥራት ያለው ትምህርት በማስተማር፣ምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ለሀገራችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያደርጋሉ የሚል እምነትም አለው። በአሁኑ ጊዜ በሂሳብና በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ስር አራት ማለትም የሂሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪና ባዮሎጂ የትምህርት ክፍሎች አሉ። ዘርፉ 73 መምህራንን እና 9 የቤተ ሙከራ ረዳቶችን ይዟል፡፡ በተጨማሪም በዘርፉ ስር 403 መደበኛና 472 የቅዳሜና እሁድ ተማሪዎችሀዋሳ፣ይርጋለም፣አለታ ወንዶና በበንሳ ማዕከላት ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ የቅዳሜና እሁድ ተማሪዎቹ በሂሳብ፣ አጠቃላይ ሳይንስና አካባቢ ሳይንስ ትምህርት ክፍሎች ውስጥ የሚማሩ ናቸው በአጠቃላይ በሂሳብና በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ስር 875 የመደበኛናቅዳሜና እሁድ ተማሪዎች አሉ።

 

የሂሳብ ትምህርት ክፍል፣ በሂሳብና በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ውስጥ ካሉት አራት የትምህርት ክፍሎች አንዱ ነው። የሂሳብ ትምህርት ተማሪዎች ጠንካራ የሂሳብ እውቀትና ክህሎት እንዲኖራቸውና በተሰማሩበት ሙያም ምክንያታዊና ውጤታማ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትትምህርት ክፍሉ ውስጥ በመደበኛ መርሃ ግብር 123 ወንድ እና 4 ሴት በድምሩ 127 ተማሪዎች በሁለተኛና በሶስተኛ አመት እየሰለጠኑ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም 26 ወንድ እና 4 ሴት በድምሩ 30 የቅዳሜና እሁድ ተማሪዎችም ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡

 

የፊዚክስ ትምህርት ክፍል በሂሳብ እና በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ውስጥ ካሉት አራት ክፍሎች አንዱ ነው። 19 ወንድ እና 1 ሴት በድምሩ 20 መምህራን እና 2 ወንድ እና 1 ሴት በድምሩ 3 የቤተ ሙከራ ረዳቶችን ያቀፈ ነው። በአሁኑ ወቅት በትምህርት ክፍሉ በመደበኛናቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብሮች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል በሂሳብና በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ውስጥ የሚገኝ ሌላኛው የትምህርት ክፍል ነው። ኬሚስትሪ፣ ከቤተ ሙከራ በሚገኝ የምርምር እውቀት ላይ የሚመሰረት ሳይንስ ነው፡፡ ትምህርት ክፍሉ 17 ወንድ መምህራንን እንዲሁም 2 ወንድ እና 1 ሴት በድምሩ 3 የቤተ ሙከራ ረዳቶች አሉት። በአሁኑ ወቅት በመደበኛናቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብሮች የሁለተኛና የሶስተኛ አመት ተማሪዎች ትምህታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡

የባዮሎጂ ትምህርት ክፍልም በሂሳብ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ስር ያለ የትምህርት ክፍል ነው።ባዮሎጂ ጉዳዮች ለሰው ልጅ ሕይወትና ሕልውና መሠረታዊ ነገሮች ናቸው፡፡ ትምህርት ክፍሉ 19 ወንድ እና 2 ሴት በድምሩ 21 መምህራንን እና 3 ወንድ የቤተ ሙከራ ረዳቶችን ያቀፈ ነው። በአሁኑ ወቅት በትምህርት ክፍሉ በመደበኛናቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብሮች ስልጠና እየሰጠ ነው።

በሂሳብ እና በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ውስጥ ያሉ የሳይንስ ቤተ ሙከራዎች በሚገባ የተደራጁና የተሟሉ ናቸው። እነዚህም ቤተ ሙከራዎች በተለያየ ምድብ የተከፋፈሉ ናቸው፡፡ በኬሚስትሪ ቤተ ሙከራዎች (አጠቃላይ፣ ኦርጋኒክና አናሊቲካል ቤተ ሙከራዎች ከግምጃ ቤት ጋር) ባዮሎጂ ቤተ ሙከራዎች  (ማይክሮ ባዮሎጂ፣ ዞሎጂ እና ቦታኒ ቤተ ሙከራዎች ከግምጃ ቤት ጋር) እንዲሁም የፊዚክስ ቤተ ሙከራዎች (አጠቃላይ፣ ኤሌክትሮኒክና ማግኔቲክ ቤተ ሙከራዎች ከግምጃ ቤት ጋር) በሚል ተለይተው አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርገዋል። ቤተ ሙከራዎቹ ትምህርቱን ተግባራዊ እንዲሆን በማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ከማድረጋቸውም በላይ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የኬሚካል ድጋፍ በማድረግ በማህበረሰብ አገልግሎት መሳተፍ እንዲቻል አግዘዋል፡፡ በተጨማሪም የኬሚስትሪ እና የባዮሎጂ ትምህርት ክፍል መምህራን 2012 በኮቪድ-19 (ኮሮና) ወረርሽኝ ወቅት የእጅ ማጽጃ (ሳኒታይዘር) በማዘጋጀት በማህበረሰብ አገልግሎት ተሳትፈዋል።

አርጊሶ ነሜሳ

የሂሳብና የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ኦፊሰር

Y2005argisonemesa@gmail.com

251913347390