Skip to main content
Image
tk

የሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በአዲሱ የትምህርት ሮድማፕ መሰረት ላለፉት 2 አመታት በቅድመ አንደኛ ትምህርት 12+2 ዲፕሎማ ደረጃ ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ወ=105፤ ሴ= 41፤ በድምሩ 146 መምህራንን በ25ኛ ዙር የምረቃ በዓል በደማቅ ስነስርዓት አስመርቋል።

በምረቃው በዓል ላይ የሲብክመ ም/ር/መስተዳድር እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ በየነ በራሳ በክብር እንግነት ተገኝተው ለተመራቂዎቹ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።

በበዓሉ ላይ የት/ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች፣ የክልሉ የመምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት፣ የአቻ ኮሌጅ ዲን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።