Skip to main content

ሰዉ ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት ዋና ዋና ተግባራት (የሚሰጣቸዉ አገልግሎቶች)-

  • ቅጥር
  • ምደባ
  • ደረጃ ዕድገት
  • የስኮላርሺፕ ዕድል
  • ዝዉዉር
  • ለአገልግሎት ፈልገዉ ለሚመጡ ተገልጋዮች በመመሪያዉና በደንቡ መሠረት አገልግሎት መስጠት
  • ድስፕሊን ማየት እና ቅሬታ ስቀርብ ከሚመለከታቸዉ አካል ጋር ማየት
  • ስንብት መስራት
  1. በስትራቴጂክ ዕቅዱ የተቀመጡትን ግቦች ለማሳካት አስፈላጊውን የሰው ሀብት በሚፈለገው ጥራት እና መጠን መመደብ፣
  2. የመምህራን ብዛት ከተማሪዎች ጋር ያለውን ጥምርታ መገምገምና ማደስ፤ እንዲሁም በግምገማው ውጤት ላይ በመመርኮዝ በዘርፉ ውስጥ ፍትሃዊ ቅጥር (ምደባን) ማረጋገጥ፣
  3. በኮሌጃችን የመምህራንና የአስተዳደር ዘርፍ የሰው ፍልሰት መንስኤዎችን መመርመር፤ የፍልሰቱ ዋና መንስኤዎች ለመፍታት አስቻይ መንገዶችን ማዘጋጀትና መከወን፣
  4. በሥራ ቦታዎች የሰው ሀብት መረጋጋትን በመጠበቅ ለትምህርት ዘርፍ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የገንዘብ እና የገንዘብ ያልሆኑ ማበረታቻዎችን መገምገምና ማጥናት፣
  5. የባለሙያዎችን ቅሬታ መመርመር፣ የቅሬታን ዋና መንስኤ ለማስወገድ መፍትሄዎችን ማዘጋጀትና መተግበር፣
  6. አስፈላጊውን አገልግሎት ለኅብረተሰቡ ለማቅረብ በተፈቀደለት የሰው ሀብት መመዘኛ መሠረት ብቁ ሠራተኞችን እንዲያቀርብ የትምህርቱን ዘርፍ መደገፍ።
  7. የሰው ሀብት የመረጃ ሥርዓትን ዘመናዊ ማድረግ፣ ለውሳኔ አሰጣጥ እና ለተሻሉ አገልግሎቶች እንዲውል ወቅታዊ ማድገረግ፣
  8. የሥራ ጫና ባለበት አድስ መደብ ለፐብሊክ ሰርቭስ በማቅብ አዲስ የፀደቀውን መዋቅር መተግበር እና ለትምህርት ዘርፍ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግን፣
  9. አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Induction) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ማድረግ፣
  10. ለዳይሬክቶሬቱ የሚያስፈልጉ ለአቅም ግንባታ ስራዎች፣ ለትምህርት፣ ለህትመት፣ ለግዥና ተያያዥ ተገቢውን በጀት በማስፍቀድ ተግባራዊ ማድረግ፤
  11. የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት የስምሪት ሥራዎች በደንብ እና መመሪያ መሠረት እንዲተገበሩ ማድረግ፣
  12. የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ ሰርኩላሮች እና አግባብነት ያላቸው መመሪያዎችን ተፈጻሚነታቸውን መተግበርና መከታተል፤
  13. የሠራተኛ የግል ማህደሮችና ማንኛውንም ሰራተኛን የሚመለከቱ መረጃ ተሟልተውና ዘመናዊ ሆነው እንዲያዙ የሪከርድና ማህደር አገልግሎት የሥራ ክፍል ክትትል ማድረግ፤
  14. የሰው ኃይል እቅድ መረጃዎች እንዲሰበሰቡ፣ እንዲደራጁ ተተንትነው እንዲጠናቀሩ ማድረግ/ማስደረግ፣ የመረጃዎችን ትክክለኝነት ያረጋግጣል፣ ለሚመለከተው አካል ተደራሽ ማድረግ፣
  15. በደረጃው ለተፈቀዱ የሥራ መደቦች የሰው ኃይል ስምሪት ፈተናዎችን እንድዘጋጅ ማድረግ/ማስደረግ፣ በሚመለከታቸው የስራ ክፍሎችም እንዲዘጋጁ ማድረግ፣ ማስፈተን/ማስተባበር፣ ማሳረም፣ እንዲታረሙ ማድረግ፣መረጃዎቹን በዘመናዊ የመረጃ ዘዴ /በሃርድና በሶፍት ኮፒ/ ተደራጅተው እንዲያዙ ማድረግ፣
  16. በዳይሬክቶሬቱ ሥር የሚገኙ ሰራተኞች በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩና ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት እንዲሰጡ ያለባቸውን የአፈጻጸም ክፍተት ይለያል፣ እንዲበቁ ማድረግ፤
  17. በሥነ-ምግባር ጉድለት ምክንያት በተከሰቱ ችግሮች ላይ በተቋቋመ ኮሚቴ ጋር በጥፋቱ ደረጃና በመመሪያ መሰረት እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግና የተወሰዱ ዕርምጃዎችን አፈጻጸም መከታተል፣
  18. የለውጥና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ቀጣይነትን የሚያረጋግጡ አዳዲስ የአሠራር ስርዓቶች በማጥናት፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ለመ/ቤቱ ጠቃሚ የሆኑትን ተግባራዊ ማድረግ፣
  19. የሥራ ዘርፉን የአሰራር ችግሮች በመለየትና በማጥናት ምቹ የአሰራር ሂደት እንዲኖር ማድረግ፣
  20. በተግባር ላይ እንዲውሉ የተመረጡ የለውጥና መልካም አስተዳደር ሥራዎች አተገባበር ከሁኔታዎች ጋር ተጣጥመው እንዲሰራባቸው ማድረግ እንዲሁም ስራ ላይ ማዋል፤
  21. በመ/ቤቱ የሚገኙ የሥራ ዘርፎች በአስቀመጡት የለውጥና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ግቦች እና እቅድ መሠረት መፈጸማቸውን ክትትል በማድረግ ለዳይሬክቶሬቱ ማቅረብ፤
  22. በመ/ቤቱ የመልካም አስተዳደር ሥርዓት መስፈኑን መከታተል፤
  23. በለውጥ አፈጻጸም ላይ የሚያጋጥሙ የአሠራር ችግሮችን በመለየት ማቅረብ፤
  24. በመ/ቤቱ ተግባራዊ የሆኑ የለውጥና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ያስገኙት ፋይዳ መከታተል፣
  25. በሥራ ላይ እንዲውሉ ውሳኔ ያገኙ ልዩ ልዩ የጥናት ሰነዶች ተግባራዊ እንዲሆኑ ለተጠቃሚ ክፍሎች ማስተላለፍ፣
  26. የለውጥና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ከአፈጻጸም አኳያ ለመገምገም በተዘጋጀ ሪፖርት አቀራረብ ስርዓት ስለመቅረቡ መከታተል፣
  27. መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር ዳይሬክቶሬቱ የሚመራበትን አዳዲስ አሰራሮች በመቀየስና በመገምገም የአሰራር ስርዓት መዘርጋት፣
  28. የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ስለለውጥ አንድ ዓላማ እንዲገነዘቡና የህዝብ አገልጋይነት ስሜት እንዲያዳብሩ የአመለካከት ለውጥ እንዲያመጡ ተከታታይነት ያላቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እንዲዘጋጁ ማድረግ፣
  29. የዳይሬክቶሬቱን ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ለበላይ አካል እና ጉዳይ ለሚመለክታቸው አካላት ሪፖርት ማቅረብ፣

          የዳይሬክቶሬቱ ደንበኞች፡-

  1. መምህራን
  2. የዲፓርትሜንት አስተባባሪዎች
  3. የስትሪም ኦፍሴሮች
  4. የአስተዳደር ዘርፍ ሠራተኞች እና ሌሎች ባለጉዳዮች

ከደንበኞች የሚጠብቅ ቅድመ ሁኔታ

 

  • ማስታወቂያ ተከታትሎ መረጃ ማግኘት
  • ለቅጥር ከሆነ በማስታወቂያዉ መሠረት ቀርቦ መመዝገብ
  • በድልድልና በምደባ ወቅት በሚገለፀዉ ጊዜ መገኘት
  • ተፈላጊ የሆኑ መረጃዎችና የድጋፊ ደብዳቤዎች ይዞ መቅረብ
  • ፈተና ካለ ቀርቦ መፈተን (ቅጥር፣ ምደባ፣ ዝዉዉር ወይም ደረጃ እድገትና ስኮላርሺፕ ሲፈልጉ)፣

  የስራ ሂደቱ የግብ ስኬት

ፈጣንና የተሟላ የቅጥር፣ የምደባ፣ የደረጃ ዕድገት መስራት፣ የስኮላርሺፕ ማወዳደር፣ ዝዉዉር፣ ድስፕሊን ማየት፣ በዕድመ ብቁነት ጡረታ የሚወጡ በድስፕሊን ጉድፈት የሚባረሩና ሌሎችም መሰናበት ለሚገባቸዉን ስንብት መስራት ሌሎች አስተዳደራዊ አገልግሎቶች የረኩ ተገልጋየች፣