Skip to main content
Image
n3
የሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ 3ኛውን አመታዊ የጥናትና ምርምር ሲምፖዚየም "ጥናትና ምርምር ለመማር ማስተማርና ማህበረሰብ ዕድገት!” በሚል መሪ ቃል ዛሬ ግንቦት 21/2017 ዓ/ም በኮሌጁ ቅጥር ግቢ አካሂዷል። በጥናትና ምርምር ሲምፖዚየሙ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ምክትል ፕሬዚደንትና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ በየነ በራሳ ባስተላለፉት መልዕክት ሀገራችን የትምህርትን አስፈላጊነት በመገንዘብ ለዘመናዊ ትምህርት ትኩረት በመስጠት ልዩ ልዩ ስራዎችን መስራት ከጀመረች ከ100 ዓመታት በላይ የተቆጠረ ቢሆንም በተለያዩ የስርአት ችግሮች ሀገርቷ የተመኘችውን ያሳካ እንዳልነበረ ተናግረዋል። ምርምር ለአንድ ሀገር ዕድገት መሰረት በመሆኑ ተመራማሪዎች ለሀገር ለውጥ ጉልህ አስተዋጽዖ በሚያበረክቱ ምርምሮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባቸውም ገልጸዋል። ምክትል ፕሬዚደንቱ አክለውም በአሁን ወቅት የሀገራችንን ወቅታዊና ተጨባጭ ችግሮችን በጥናት በመለየትና በመረዳት አዲስ የትምህርት ፖሊሲ ተቀርጾ ወደ ተግባር መገባቱን አስታውሰው እንደ ሲዳማ ክልል የሚስተዋሉ የትምህርት ሴክተር ችግሮችን በመለየት ክልላዊ የትምህርት ተሐድሶ ፕሮግራም በመቅረጽ ወደ ተግባር እንደተገባና አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ አክለውም ኮሌጁ በመማር ማስተማር፣ ምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ተልዕኮውን ለመወጣት እያከናወነ ያለው ሥራ አበረታች መሆኑን አንስተው የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።